ቡታጅራ፤ ጥር 21/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር እየተመቻቸ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ዛሬ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንዳመለከቱት፤ በክልሉ የሚገኙ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ተገልጋዩ በቦታ ሳይገደብ ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ጥረት እየተደረገ ነው።
ተቋማት የሚያከናውኗቸው ሥራዎች እና የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በድረገፅ እንዲያስተዋውቁ 15 ድረ-ገፆችን ማልማት መቻሉን ተናግረዋል።
በተለያዩ ተቋማት የሚደረጉ ስብሰባዎችን በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲከናወኑ በማድረግ ወጪን መቆጠብ መቻሉንም ገልጸዋል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተገነባ ተቋምና የሰው ኃይልን ማመቻቸቱን በመቀጠል በሁሉም መስክ ክልሉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚሰራም ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በበኩላቸው፤ በዞኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ከማሳደግ አንጻር ለውጥ እየመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በዞኑ የፈጠራ ስራዎችን ከማበረታታት አንፃር ከ20 በላይ ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ የፈጠራ ስራዎች እውቅና ማግኘት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡
በከተማው ተቋማት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የገለጹት ደግሞ የወራቤ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ባርሰባ ናቸው።
ተግባሩን አጠናክሮ በማስቀጠል በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የዞንና የልዩ ወረዳ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025