
ወልዲያ፤ ጥር 28/2017 (ኢዜአ)፦ በወልዲያ-ቆቦ መንገድ የሚገኘው የአሚድ ወንዝ ብረት ድልድይ በመሰበሩ ድልድዩን በሌላ ለመተካት ጥረት እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።
በድልድዩ መሰበር ሳቢያ የተስተጓጎለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር በጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት ተለዋጭ መተላለፊያ መንገድ መሰራቱን አስታውቋል።
በአስተዳደሩ የድልድዮችና ስትራክቸር ክፍል ዳይሬክተር ኢንጂነር ተክለስላሴ ንዳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ትናንት ከሰዓት የአሚድ ወንዝ ብረት ድልድይ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ የጫነ ተሽከርካሪ ሲሻገር የብረት ድልድዩ ተደርምሷል።

በስፍራው የተፈጠረውን ትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎል ለመፍታት አስተዳደሩ የግንባታ ማሽኖች ወደ ስፍራው ልኮ ተለዋጭ መንገድ በመስራት ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠቱን ገልጸዋል።
በዚህም አነስተኛ ተሽከርካሪዎች በተለዋጭ መተላለፊያ መንገድ አገልግሎት እየሰጡ መሆን ገልጸዋል።
የብረት ድልድዩን በሌላ በመተካት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትም አስተዳደሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ከወልዲያ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የአሚድ ወንዝ ድልድይ 48 ሜትር ርዝመት ያለው የብረት ድልድዩ ነው።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026