አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት 471 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ።
አስተዳደሩ የመንገዶችን ጥራትና የኮንስትራክሽን ሂደት በቅርቡ ለመከታተል በተመረጡ አካባቢዎች ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ እየሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚዛን አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላዬ ንጋቱ ገልጸዋል።
በክልሉ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት የሚዛን-ቴፒ፣ የሺሺንንዳ-ቴፒ፣ ጎሬ-ማሻ-ቴፒ፣ ኩቢጦ ማዞሪያ እና መቱ ከተማ የሚከናወኑ 6 የአስፓልት መንገዶች እንደሚገኙበት ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
በክልሉ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት እየተከናወነ ከሚገኘው የ471 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ሥራ የሚዛን ቴፒ አንዱና ከተጀመረ ረዘም ያለ ጊዜን የወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል።
አካባቢው ዝናባማ በመሆኑ ያለውን አጭር ጊዜ ለመጠቀም ርብርብ እየተደረገ ሲሆን እስካሁን ባለው ከሚዛን ቴፒ 48 ኪሎ ሜትር የአምናውን ጨምሮ 15 ኪሎ ሜትር መንገድ አስፓልት በማልበስ ወደ 20 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የጎሬ ማሻ ፕሮጀክት በዚህ በጀት ዓመት 20 ኪሎ ሜትር የተከናወነ ሲሆን ወደ 50 ኪሎ ሜትር ለማድረስ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አቶ ጥላዬ ገልፀዋል።
በአስፓልት መንገድ ግንባታው የየኪ፣ የሸኮ ወረዳዎችና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአዲሱ አዋጅ መሠረት የወሰን ማስከበር ስራው በሚፈለገው መንገድ የሚሄድ ከሆነ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ ይሰራል ብለዋል።
በዚህም ከሚዛን ቴፒና ከቴፒ ማሻ ጎሬ ያለው የአስፓልት መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ የሚዛን ዲማ ደግሞ በቀጣይ እንዲጠገን ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።
የቻይና CCG ግሩፕ ኮንተራክተር ፕሮጀክት ማናጀር ሚስተር ዞ፤ እአአ 2018 የተጀመረው የመንገድ ፕሮጀክቱ የተለያዩ ችግሮች በማጋጠሙ መዘግየቱንና አሁን በተደረገው ጥረት የሚዛን ቴፒ 60 በመቶ በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት 20 ኪሎ ሜትር ለማጠናቀቅ አቅደው 12 ኪሎ ሜትር እንዳደረሱና ቀሪውን ለመጨረስ አስፈላጊውን ማሽኖች በመጨመር ርብርብ እንደሚደረግ ጠቁመው የአካባቢው መስተዳድሮች ወሰን ማስከበር ላይ ድጋፍ እንዲያደረጉ ጠይቀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025