የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>ባለፉት የለውጥ አመታት በቤት ልማት ዘርፍ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ አበረታች ውጤት ተገኝቷል</p>

Feb 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ጥር 29/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት የለውጥ አመታትበቤት ልማት ዘርፍ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ አበረታች ውጤት መገኘቱን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከፖሊሲ ጥናት ኢኒስትቲዩት ጋር በመተባበር ባከናወነው የቤት ፋይናንስ ስርዓት ዝርጋታ የጥናት ማጎልበቻ ዙሪያ ያጠነጠነ መድረክ ዛሬ ተከናውኗል ፡፡

ስርዓቱ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገትን፣ በማጎልበት እና ድህነትን በመቀነስ ዜጎች ቋሚ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል፡፡

በዚሁ ወቅት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ሔለን ደበበ ባለፉት የለውጥ አመታት በቤት ልማት ዘርፍ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን በአጠቃላይ በከተሞች ካለው የቤት ፍላጎት አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለሟሟላት ከቤት ፋይናንስ፣ ከአልሚዎች፣ ከመሬት ልማትና አቅርቦት ተቋማት፣ ከከተማ ፕላንና፣ ከዘርፉ ሙያተኞች ጋር ቅንጅት በመፍጠር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ በቤት ፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት ተግዳሮት ሆኖ የቆየው የቤት ፋይናንስ እጥረት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ ረገድ የመኖሪያ ቤት ፍላጎቱን በመሙላት አቅርቦቱን ለማሳለጥ ራሱን የቻለ የቤት ፋይናንስና ምንጭ የአቅርቦት ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ሚኒስቴሩ የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ለውይይት ክፍት ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

የቤት ልማት የፋይናንስ ስርዓቱ በዋናነት የፋይናንስ ምንጮችን መለየት፣ የመኖሪያ ቤት ልማት ፋይናንስ የአቅርቦት ስርዓት አስተዳደርና አሰራር ዘዴን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026