
ጋምቤላ፤ ጥር 29/2017 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።
የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች ከማስተዋወቅ ባለፈ ኢንቨስተሮቹ ምርትና አገልግሎታቸውን ለዕይታ ሚያቀርቡበት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ዛሬ በጋምቤላ ተጀምሯል።

የሁነቱ አካል የሆነ የፓናል ውይይት ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በተሳተፉበት እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ያሉትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ልማት ለማስገባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
በክልሉ ለኢንቨስትመንት ልማት የሚውል ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት ቢኖሩም በተፈለገው ደረጃ ባለመልማቱ ህዝቡ ከዘርፉ በተገቢው ተጠቃሚ ሳይሆን እንደቆየ ተናግረዋል።
በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት እንደ ክልል ብሎም እንደ አገር የታለውን የኢኮኖሚ እደገት እውን ለማድረግ ከባለሃብቱ የላቀ አበርክቶ ይጠብቃል ብለዋል።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከሚፈጥሩት የስራ እድል በተጨማሪ የአካባቢውን አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና የምግብ ዋስተናቸውን እንዲያረጋገጡ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ከለውጡ በፊት በክልሉ ሲስተዋሉ የነበሩት ያልተገቡ አሰራሮች በኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደነበራቸው አስታውሰዋል።
የክልሉ መንግስት ችግሮችን በማስተካከል የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲነቃቃ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
በዚህም በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በክልሉ ለሚሰማሩ አልሚ ባለሀብቶች የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ይቀጥላል ብለዋል።
ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫሉ አዳዲስ ባለሀብቶችን ለመሳብና ነባር ባለሀብቶችን እንደሚያነቃቃ ጠቁመዋል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ(ዶ/ር) በበኩላቸው የክልሉን ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም በማልማት ከዘርፉ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።
ዐውደ ርዕዩ የክልሉን ጸጋዎች በማስተዋወቅ ክልሉን ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026