
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በግምገማችን ባለፉት ስድስት ወራት መገንባት የጀመርነውን ጠንካራ የስራ ባህል የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር እንዲሁም የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት አጠናቀን ለህዝባችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የሀገርን ክብር በሚመጥን መልኩ ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ አዲስ አበባን አለም አቀፍ የስበት ማዕከል ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪዎቻችን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እና ሰፊ የስራ እድል የፈጠሩ፣ አገልግሎትን የሚያሳልጡ ተግባሮች ተከናዉነዋል፣ የተቀሩትንም በቀሪ ወራት በፍጥነት የምናጠናቅቅ ይሆናል ነው ያሉት።
በቀጣይም የአፈፃፀም ዉስንነትን በማስተካከል፣ ማዘመን የጀመርነዉን አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር ቀልጣፋ እና ፈጣን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተደራሽ በማድረግ፣ ብልሹ አሰራር እና ጉቦኝነትን በመታገል እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።
ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ድክመቶቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲታረሙ እያደረግን ለላቀ ውጤታማነት መትጋታችንን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026