የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>የንግድ ትርኢትና በዛር በደብረ ብርሃን ከተማ ተከፈተ</p>

Feb 11, 2025

IDOPRESS

ደብረብርሀን ፤ የካቲት 3/2017 (ኢዜአ) ፡- አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ለማቅረብ የተዘጋጀ የንግድ ትርኢትና በዛር በደብረ ብርሃን ከተማ ተከፈተ።

በዝግጅቱ ከ150 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የተደራጁ ወጣቶች መሳተፋቸው ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት፤ የንግድ ትርኢትና ባዛሩ አምራቹን ከሸማቹ ማህበረሰብ ጋር በቀጥታ በማገናኘት የዋጋ ጭማሪን ለመቀነስ ያለመ ነው።

የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በብዛትና በጥራት በማቅረብ ህብረተሰቡ የመግዛት አማራጩ እንዲሰፋ የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የደብረ ብርሃን ንግድ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ይርጋለም ምስጋናው በበኩላቸው፤ የንግድ ትርኢትና ባዛሩ በግብርናና በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።


በዚህም ከ150 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የተደራጁ ወጣቶች መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።

ዝግጅቱ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ለማጎልበት እንደሚረዳ የገለጹት የደብረ ብርሃን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ አማረ ገብረ ዮሀንስ ናቸው።

በተጨማሪም በአንዳንድ ህገ ወጥ ነጋዴዎች የሚስተዋለውን ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ለመከላከል እንደሚያግዝ ጠቁመው ፤ የምክር ቤቱን ህንጻ ለማስገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉም አካል እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።


የወደራ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን የግብርና ምርቶች የግብይት ክፍል ሃላፊ አቶ ወርቁ ባዘዘው እንዳሉት፤ ዩኒዬኑ ከአምስት ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ፣ ማሽላና የተለያዩ የጥራጥሬ ሰብሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቧል።

የንግድ ትርኢትና ባዛሩ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ከከተማ አስተዳደሩ ንግድ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026