የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን የመቆጣጠሩ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል</p>

Feb 14, 2025

IDOPRESS

አርባ ምንጭ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት በሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ ገለጹ።

በክልሉ ከ49 ሚሊዮን 552 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ህገ-ወጥ ነዳጅ መያዙም ተመልክቷል።

በነዳጅ ምርቶች አዋጅ፣ በአቅርቦትና ስርጭት ላይ ያተኮረ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ በተካሄደበት ወቅት አቶ አለማየሁ እንዳመለከቱት፤ በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ችግር እየፈጠረ ነው።


ህብረተሰቡን እየጎዱና ለመልካም አስተዳደር ችግር እያጋለጡ ያሉ የነዳጅ ማደያዎችን በመለየት ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገሌቦ ጎልቶሞ በበኩላቸው፤ መንግስት በከፍተኛ ድጎማ ነዳጅን ከውጭ ቢያስገባም ለዘርፉ ቅርበት ያላቸው አካላት የግብይት ሰንሰለቱን በማዛባት ተግዳሮት እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ ተሰማርተው ህዝብን ለችግር እያጋለጡ ያሉትን አካላት ለመከላከል በተደረገው ጥረት ከ49 ሚሊዮን 552 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ህገ-ወጥ ነዳጅ መያዙን ጠቅሰዋል።

በህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ ሲንቀሳቀሱ በተገኙ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው በበኩላቸው፤ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመከላከል በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክ የክልሉና የዞን የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የፀጥታ አካላትና ሌሎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በአዲሱ የነዳጅ ግብይት አዋጅ ላይም ግንዛቤ የማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄዷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026