አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፡- በአፍሪካ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስርን ለማሳለጥ የመሰረተ ልማት ግንባታን ማጠናከር እንደሚገባ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ዚ ቻሩሚቢራ ተናገሩ፡፡
በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የፓን አፍሪካ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ዚ ቻሩሚቢራ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ጉባኤው በወሳኝ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣናን እውን በማድረግ የአህጉሪቱን ህዝቦች ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መወያየቱ ወሳኝ እና አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት የንግድ ልውውጥ መጠናከር የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ስለሚያሳድግ ጉዳዩ ትኩረት ማግኘቱ ተገቢ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረግ የንግድ ልውውጥ ከፍተኛ እድገት የሚያመጣ መሆኑን አመልክተው፤ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ይበልጥ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የንግድ ልውውጥ የሰዎችን ነጻ ዝውውር የሚፈልግ መሆኑን አመልክተው፤ ለስኬታማነቱ የሀገራት መሪዎች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ተናግርዋል።
ለአንድ ሀገር እድገት ሰላም ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የአፍሪካ ሀገራት ለሰላም ግንባታና ውጤታማነት መስራት እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት ሰላምንና ደህንነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና የሚኖረው ስትራቴጂ መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025