
ጅማ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የአምስተኛውን ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ዛሬ አስጀመረ።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩና የኩባንያው ከፍተኛ አመራር አባላት እንዲሁም የጅማ ከተማና የጅማ ዞን አመራሮችና የአገልግሎቱ ደንበኞች ተገኝተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኩባንያው አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ጉዞ ላይ ነው።
የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት የዓለማችን ፈጣንና ቀልጣፋ የኔትወርክ አገልግሎት መሆኑን አንስተው አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በ12 ከተሞች አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ደንበኞች ዘመኑን የሚመጥን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬ በጅማ የተጀመረው የአምስተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በከተማዋና በአካባቢው የሚከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን በተሻለ ደረጃ ለመከወን የሚያግዝ ነውም ብለዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026