
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጎነት መንደር የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላልፈዋል።
ዛሬ ለነዋሪዎች የተላለፉ ቤቶቹ በልደታ ክፍለ ከተማ በበጎነት መንደር የተገነቡ ሁለት ባለ ዘጠኝ ወለል የመኖሪያ ህንፃዎች ላይ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የከተማዋን እድገት እና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ በተባበረ ክንድ ከሰራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል።

ከተማ አስተዳደሩም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጀቱን በአግባቡ ተግባር ላይ በማዋልና ህዝቡን በንቃት በማሳተፍ የሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም በአስቸጋሪ የመኖሪያ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ እንዳሉት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እና ምቹ ባልሆኑ መኖሪያዎች ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መኖሪያ ቤት መኖር እንዲችሉ ለማድረግ በሚሰሩ ተግባራት ባለሀብቶች ላደረጉት እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመቅረፍ በሚደረጉ ጥረቶች ግሩፑ የነቃ ተሳትፎ በማድረጉ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።
የመኖሪያ ህንፃዎቹ ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋራ በመተባበር የተከናወነ መሆኑም ተጠቅሷል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026