
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በሀረሪ ክልል ባለፉት ዓመታት በከተማ እና ገጠር ፍትሀዊ የሆነ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት እንዲኖር የማስቻል ስራ መሰራቱ ተገልጿል።
በክልሉ በተለይም ወረዳን ከወረዳ ብሎም ገጠሩን ከከተማ ጋር የሚያገናኙ የአስፓልት እና የጠጠር መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውም ተመላክቷል።

ይህም አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ ማቅረብ እንዲችል እና የጉልበት የሃብትና የጊዜ ብክነትን ማስቀረት ማስቻሉም ተገልጿል።
የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የአካባቢን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር የአካባቢውን ኢኮኖሚ እንዲነቃቃም በማሳደግ ረገድ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ይገኛል።
በዘንድሮው የበጀት አመትም ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ለመንገድ ፕሮጀክት ተመድቦ እየተሰራ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026