
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የደረሰኝ ልዩ መለያ ኮድ ወጥ፣ ዘመናዊና ፍትሐዊ የግብር አሰባስብ ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ።
መንግስት ከሕገ ወጥ ደረሰኝ ሕትመትና ስርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን ጉድለት የሚሸፍን ዘመናዊና ፍትሃዊ የሆነ የታክስ ስርዓት ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ነው።
ገቢዎች ሚኒስቴርም ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ፎርም ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ልዩ መለያ ኮድ የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ነጋዴዎች ስራ ላይ እንዲያውሉትም የማድረግ ስራ ተግባራዊ ተደርጓል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የመረጃና ቴክኖሎጂ ማዕከል ኃላፊ አቶ ክልሉ ታመነ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለመገንባት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ሚኒስቴሩ ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ፎርምይፋ ማድረጉ እንደ ማሳያ ጠቅሰዋል።
ይህም ሕገ ወጥ የደረሰኝ ህትመትና ስርጭት በማስወገድ በዘርፉ አስተማማኝ የቁጥጥር ስራ ለማከናወን ያግዛል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪም ልዩ መለያ ኮዱ ዘመናዊና እና ፍትሃዊ የሆነ የታክስ አሰባሰብ ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ታህሳስ ወር ላይ ደረሰኞቻቸውን ወስደው ወደ ስራ መግባታቸውንም አንስተዋል፡፡
አሁንም ተግባራዊ ያላደረጉ ነጋዴዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ወደ ስራ ያልገቡትን ለማስገባት ደረሰኝ የማሳተሚያ ጊዜውን እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲራዘም መደረጉን ጠቅሰዋል።
ነጋዴዎችም የተራዘመውን ጊዜ በመጠቀም ደረሰኞቻቸውን ወስደው ወደ ስራ መግባት እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026