
ገንዳ ውሃ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በመተማ ከተማ የተገነባው የእንስሳት ማቆያን/ኳራንታይን/ ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ።
የእንስሳት ኮንትሮባንድ ንግድ መከላከል ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ በገንዳ ውሃ ከተማ ተካሂዷል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌትነት በሊሁን በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ዞኑ ጠረፋማ በመሆኑ በአብዛኛው ለኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ የተጋለጠ ነው።
በአካባቢው ያለውን የእንስሳት እምቅ ሃብት በህገ ወጥ ነጋዴዎች አማካኝነት እየባከነ መሆኑን ተናግረዋል።
ችግሩን ለማቃለል በ30 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን የእንስሳት ማቆያ ወደ ስራ ለማስገባት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የተቀናጀ ጥረት እየደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃለፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ እንዳሉት፤ ዞኑ ለወጭ ንግድ ከሚመረተው ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ጥጥና ሌሎች ምርቶች ባሻገር ሰፊ የእንስሳት ሀብት ባለቤት ነው።
በፀጋው ልክ በመስራት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ ለዚህም ህገወጥ የቁም እንስሳት ንግድን ለመከላከል የሚያግዝ ማቆያው(ኳራንታይኑ) ስራ እንዲጀምር ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማቆያው (ኳራንታይኑ) ስራ አስኪያጅ ፀጋዬ ብርቱዓለም(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ማቆያው(ኳራንታይኑ) የተሟላ የሰው ኃይልና ግንባታ ያለው በመሆኑ ወደ ስራ መግባት ለሚፈልጉ ላኪዎች የፈቃድ ማረጋገጫ መስጠት እንደሚቻል አብራርተዋል።
የመተማ ዮሃንስ ጉምሩክ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አማረ ብርሌ በበኩላቸው፤ የቁም እንስሳት ኮንትሮባንድን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 318 የቁም እንስሳት ወደ ውጭ ለማሻገር ሲሞከር መያዙን ጠቅሰው፤ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር እንቅስቃሴውን ማስቆም ይቻላል ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የዞኑ፣ የከተማ አስተዳደር አመራር አባላት፣ የጉምሩክ ስራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026