ጅማ፣ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፦ ምሁራን ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ብሔራዊ ጥቅም የሚበጁ የስትራቴጂና ፖሊሲ ግብዓት ምክረ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ ተጠየቀ።
“አገራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለህዝቦች ሚዛናዊ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሃሳብ በሰላም ሚኒስቴርና ጅማ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ የምሁራን የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት (ዶ/ር) ጀማል አባ ፊጣ ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚሻ ጠቅሰዋል።
ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥም የምሁራን ተሳትፎ የላቀ ነው ብለዋል።
የመነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር ኢድሪስ የባ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ከብሔራዊ ጥቅምና ከቀጣናዊ ትስስር ጋር መቃኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ቀጣናዊ ትስስርን ለፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል፣ ማህበራዊ ፍትህና ኢኮኖሚያዊ እመርታ ካለው ፋይዳ አኳያ ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
በዚህም ምሁራን ጥናትና ምርምር በማካሄድ የስትራቴጂና ፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን በማቅረብ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በሰላም ሚኒስቴር የሀገር ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀለፎም አባይ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ምሁራንን ለሀገርና ህዝብ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ ምቹ መደላድል አመቻችቷል ብለዋል።
የውይይት መደረኩ የሀገር ብሔራዊ ጥቅም ከቀጣናዊ ትስስር አኳያ ያለውን ሁሉን አቀፍ ፋይዳ ለመቃኘት ያለመ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።
በሀገሪቱ ሰላምን በማስፈን ልማትን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ቀጣናዊና አለም አቀፋዊ ግንኙነት ለማጎልበት የፖሊሲ እና የስትራቴጂ አቅጣጫዎችን ለመከተል ያግዛል ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025