አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔን በተቀናጀ መልኩ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ።
በመጪው ሐምሌ ወር 2017ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔን በስኬት ለማስተናገድ በተጀመሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ጉባዔውን በተቀናጀ መልኩ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረጉ ያሉ ተግባር ተኮር እና ለውጥ ያመጡ ሥራዎችን በተመለከተም ገለፃ አድርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በርካታ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሰዋል።
ሐምሌ ወር በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ጉባኤም ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በመጠቀም የተሟላ ዝግጅት እንደምታደርግ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልዑካን ቡድን መሪ እስጢፋኖስ ፎሽው(ዶር) ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመንግሥት እየተከናወነ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማድነቅ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ እንደምታስተናግድ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
በዚህ የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት የኮሜቴ ውይይት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቋማት እና በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ተጠቅሷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025