
ደሴ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የአምስተኛው ትውልድ(5ጂ) ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ።
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ ከፍትኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎትን እውን የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ኢትዮ ቴሌኮም በሁሉም አካባቢዎች የአምስተኛው ትውልድ(5ጂ) ኔትወርክ እንዲስፋፋ አበክሮ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
የአገልግሎቱ መጀመር የኔትወርክ አቅምን ከመጨመር ባለፈ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራልም ብለዋል።
በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በትራንስፖርት፣ በቱሪዝምና ለሌሎች ዘርፎች አገልግሎቱ የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑንም አብራርተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በጅማ ከተማ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026