
ድሬዳዋ፣ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሐ ግብር የታቀፉ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን የስራና ከህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ።
በሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የፌደራልና የአስተዳደሩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን በድሬዳዋ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን የመስክ ግምገማ አድርጓል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት ህብረተሰቡን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተለያዩ መርሐ ግብሮችን ገቢራዊ እየተደረጉ ስለመሆኑ ጠቅሰው፤ ልማታዊ ሴፍቲኔትን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር በዚሁ መርሐ ግብሩ የታቀፉ የማህበረሰብ ክፍሎች በተደረገላቸው ድጋፍ ወደ ምርታማነት እየተሸጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የመስክ ምልከታው በድሬዳዋ አስተዳደር ሲጠናቀቅ በቀጣይ በሐረሪ ክልል እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026