የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን በልማት የማስተሳሰሩ ስራ እንደሚጠናከር ተገለጸ</p>

Feb 25, 2025

IDOPRESS

አሶሳ ፤ የካቲት 17/2017(ኢዜአ):- ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን በልማት የማስተሳሰሩ ስራ እንደሚጠናከር የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ በ225 ሚሊዮን ብር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ የተገነባው የባሮ ኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።


የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በወቅቱ እንደተናገሩት የሁለቱን ክልል ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የትብብር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ሁለቱ ክልሎች ከዚህ በተሻለ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ያላቸው ትስስሮች እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

''በአንድነት እና በመተጋገዝ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው'' ያሉት አቶ ሽመልስ፤ ለዚህም ማሳያው የሁለቱ ክልሎች የጋራ ልማት ነው ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው የሁለቱ ህዝቦችን የቆየ ወዳጅነት በልማት ስራዎች ለማስቀጠል የተጀመረው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግም የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

''በህዝቦች መካከል ፀንቶ የቆየውን አብሮነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለሌሎችም ተሞክሮ ለማድረግ እንሰራለን፤ ይህም ይጠናከራል'' ብለዋል።

''ትምህርት ቤቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አጋዥ ይሆናል'' ያሉት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026