
ቡታጅራ፤ የካቲት 18/2017 (ኢዜአ) :- የግብርና ምርምር ተቋማት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በስፋት ተደራሽ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለጸ።
የክልሉ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች በተመለከተ በቡታጅራ ከተማ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ፤ በግብርናው ዘርፍ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
የግብርና ምርምር ተቋማት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የእንስሳትና የሰብል ዝርያዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የክልሉ የግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፀጋዬ ተረፈ፤ የግብርናውን ዘርፍ የሚያግዙ በርካታ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ ተደራሽም እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ምርምር ተቋማቱ በተለይም በሰብልና የእንስስት ዝርያ ማሻሻል ላይ አተኩረው እየሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል።
ለአብነትም በሽታና ድርቅን መቋቋም የሚችሉና ምርታማ የሆኑ በስንዴ ሰባት እንዲሁም በባቄላ ሶስት ዝርያዎች በማፍለቅ የተሰበሰበ ከ3 ሺህ 200 ኩንታል በላይ የቅድመ መስራችና መስራች ዝርያዎች መሰራጨቱን ተናግረዋል።
በእንስሳት ልማትም የተሻሻሉ የወተትና ስጋ ከብቶች እርባታ ላይ ውጤታማ የምርምር ስራዎች ተከናውነው ለአርሶ አደሮች ተደራሽ እየተደረጉ ነው ብለዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው መድረክ 49 ያለቁና 109 በሂደት ላይ ያሉ እንዲሁም 302 አዳዲስ የምርምር ውጤቶች እንደሚቀርቡም ይጠበቃል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026