የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የአፍሪካን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማቀላጠፍ ሀገራት የተግባር እርምጃ መውሰድ አለባቸው

Feb 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማቀላጠፍ ሀገራት በትብብር ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 'ኤክስቴንሲያ' ከተሰኘ ሁነት አመቻች ጋር ያዘጋጀው የተቀላጠፈ የዲጂታል ሽግግር 2025 ስብሰባ "አዳዲስ ዕድሎችን መጠቀም" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ የተቀላጠፈ የዲጂታል ሽግግር 2025 ስብሰባ የአፍሪካን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወስን ነው።

መርሐ ግብሩ የፓን አፍሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ተቆጣጣሪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ባለሀብቶች የአፍሪካን የዲጂታል ሽግግር ለማቀላጠፍ ተሰባስበው የሚመክሩበት መሆኑን ገልጸዋል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ የአፍሪካን ኢኮኖሚ መልክ የሚቀይር፣ የአዲስ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር እና አፍሪካ በዓለም ገበያ ላይ ያላትን ድርሻ የሚወስን መሆኑንም ጠቁመዋል።

የዲጂታል አገልግሎት፣ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚ ለመገንባት አይ ሲ ቲን መሰረት ያደረጉ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት እና አካታች እድገት ለማስመዝገብ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም የዲጂታል ሽግግርን እውን ለማድረግ ከንግግር ያለፈ የተግባር አንድነት፣ትብብር እና ቆራጥ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።

የአፍሪካ ትልቁ ጸጋ ጥሬ እቃ ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሩቅ አሳቢ መሪዎች፣ የብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች፣ስራ ፈጣሪዎች ጭምር መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በሁሉም ማዕዘናት በጋራ በመስራት አፍሪካን መቀበል ብቻ ሳይሆን መሪ የምናደርግበትን እድል በአፋጣኝ መጠቀም ይገባናል ብለዋል።

የዲጂታል ሽግግር 2025 ስብሰባን በተባባሪነት ያዘጋጀው የኤክስቴንሲያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታሪቅ ማሊክ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በሳይንስና ቴክኖሎጂ እመርታዊ እድገት አስመዝግባለች ብለዋል፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ ገቢራዊ በማድረግ በማህበራዊ ፤ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ተጨባጭ ውጤት ማምጣቷንም ገልጸዋል፡፡

መንግስት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማዘመኑ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማደጉን ገልጸው፥ ይህም ለዲጂታል ሽግግር ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያዎች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽ

ሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር)፥የተቀላጠፈ የዲጂታል ሽግግር 2025 ስብሰባ የአፍሪካን ዲጂታል ስትራቴጂን ለማሳካት አጋዥ ሁነት ነው ብለዋል፡፡

መድረኩ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ የምታካፍልበት ከሌሎች ሀገሮች የምትማርበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025