የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማትን አገልግሎት ማዘመንና ተደራሽነት ማስፋት ይገባል</p>

Feb 27, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ የካቲት 19/2017 (ኢዜአ)፦ በክልሉ የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመንና ተደራሽነትን ማስፋት እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለፁ።

የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም በነባርና በአዳዲስ የስራ መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዐውደ ጥናት ዛሬ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የጋምቤላ ክልል አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ ጋትሉክ ሮን (ዶ/ር) እንዳሉት አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማትን አገልግሎት ማዘመንና ተደራሽነት ማስፋት ይገባል

የብድርና ቁጠባ ተቋም አገልግሎትን በማሻሻል የስራ አጥ ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት እየተከናወነ ያለውን ስራ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።

ተቋሙ ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ተቋማዊ አደረጃጀቱን ማሻሻልና ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ታግዞ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በተለይም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን የዜጎችን የብድርና ቁጠባ ፍላጎት ለማርካት ነባርና አዳዲስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት መጠናከር ያለበት ነው ብለዋል።

ተቋሙ የዜጎችን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ ብድር በመስጠት ወጣቶችን ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጋምቤላ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም ኃላፊ አቶ ኡቻን ኡቻን በበኩላቸው የክልሉ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም የፋይናንስ አካታችነትን በመከተል ስራ አጥ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

በተለይም ተቋሙ የገንዘብ አቅሙን በማጠናከር ዘላቂ፣ ተደራሽና ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዛሬው ዐውደ ጥናት ዓላማም ባለድርሻ አካላት በተቋሙ አዳዲስ መመሪያዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የአጋርነታቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

በዐውደ ጥናቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ የቦርድ አባላት፣ የዞንና የወረዳ የዘርፉ አመራሮችና አጋር አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026