
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ሕገ ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠርና የምርት አቅርቦትን በማሻሻል ገበያውን የማረጋጋት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ::
ሚኒስትሩ ከሸቀጦች አቅርቦት እና ገበያውን ከማረጋጋት ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለሸቀጦች ዋጋ መናር ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ዋነኛው በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የግብርና ምርቶችን ጨምሮ መሰረታዊ ሸቀጦችን በተለያዩ አማራጮች ለህብረተሰቡ የማቅረብ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመላ ሀገሪቱ ወደ ሥራ በገቡ 1 ሺህ 234 የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ለሸማቾች ምርቶችን የማቅረብ ስራዎች አበረታች ውጤቶች እየታየባቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ዘመናዊ የገበያ ማዕከላትን ወደ ሥራ በማስገባትም የተለያዩ የግብርና ምርቶች በቀጥታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች የሚቀርብበት ሂደት ሌላው ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት ነው ብለዋል።
የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የአትክልትና እንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች በተሻለ መልኩ ለዜጎች እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከምርት አቅርቦት ጎን ለጎን ምርትን በመደበቅ፣ ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር እንዲሁም የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።
በሌላ በኩል መንግሥት በከፍተኛ ወጪ የሚያስገባውን የነዳጅ ምርት ስርጭት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል።
ህገ ወጥ ድርጊት በሚፈጽሙ አካላት ላይም የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026