
መቀሌ፤ የካቲት 21/2017 (ኢዜአ)፦ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር በሚያሰራጩ አካላት ላይ ቁጥጥር እና የሕግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎች ዓለም ላይ ፈተና እየሆኑ መምጣታቸው ችግሩን ለመከላከል አገራት የየራሳቸውን ጥረት እያደረጉ ነው።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጭን ሃሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ለመከላከል መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህርና የስነ-ህዝብ ተመራማሪ ዳንኤል ግርማይ፤ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችና ጥላቻ ንግግሮች ለግጭትና አለመረጋጋት መንስዔ እንደሆኑ አንስተዋል።
በተለይም በውጭ አገራት ተቀምጠው ሀሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮችን በስፋት የሚያስተጋቡ አካላት እንዳሉ ጠቁመዋል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለሀገር ልማትና የህዝብ ተጠቃሚነት በሚበጁ አወንታዊ ተግባራት መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል።
ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች መጠበቅ እንደሚገባቸው ጠቅሰው፤ በአንጻሩ መንግስት ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ መምህር ገብረእግዚአብሄር ሀፍቱ፤ በርካታ ተከታይ ያላቸው አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተዋኒያን ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን እንደሚያስተላለፉ ገልጸዋል።
በመሆኑም ሀሰተኛ መረጃዎች ሰላምን የሚያውኩ አካላትን ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ እና የሕግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026