ሆሳዕና፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የማህበረሰብ ጥሪት ግንባታና የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ትግበራ መገባቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) አስታወቁ።
በሁለት ዓመታት ውስጥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማሸጋገር የሚያስችል ግብ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የማህበረሰብ ጥሪት ግንባታና የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ፕሮጀክት እቅድ ላይ የሚመክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሻው(ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ምርታማነትን ማሳደግ የሚስችል ዕቅድ ተዘጋጅቷል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት በማቋቋም ከተረጂነት ለማውጣት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መንግሥት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ለማሳካት ተረጂ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችል የበጀት ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የሚያስችልና ተፈፃሚ የሚሆን የፕሮጀክት እቅድና የበጀት ድልድል ለ35 ወረዳዎች መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ከግብ ለማድረስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ማዕረጉ ማቲዎስ በበኩላቸው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመረው ጥረት እውን እንዲሆን በክልሉ የሚገኙ ተረጂዎችን ያሉበትን ደረጃ የማጥራት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት በማቋቋም ከተረጂነት እንዲወጡ ማድረግ የሚያስችል እቅድ መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ በሚገኙ 35 ወረዳዎች በተለይም ግብርናን መሰረት ባደረገ የስራ መስክ ለማሰማራት በጀት መመደቡንና ለተግባሩ ተፈፃሚነት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መፈፀሙን አስታውቀዋል።
በመርሐ ግብሩ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራር አካላት ተሳተፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025