የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>ሀገራዊ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር 9 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር ደርሷል</p>

Mar 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ ከአራት ዓመት በፊት ከ50 ቢሊዮን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር ወደ 9 ነጥብ 7 ትሪሊየን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን ገቢራዊ የተደረገውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ቀድሞ ማሳካት ተችሏል፡፡

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ግብ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ በመሆኑ ስትራቴጂውን ቀድሞ ማሳካት እንዳስቻለ ጠቁመዋል።

በዚህም በተቀመጡ ቁልፍ መለኪያዎች መሰረት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ቀድመን እየጨረስን ነው ብለዋል፡፡

ከመታወቂያ አገልግሎት ጀምሮ የግብይት ሥርዓቱ በቴሌ ብር፣ በሞባይል ባንኪንክ እና በሌሎች ዲጂታል አማራጮች እየተለመደ መምጣቱን አንስተዋል።

የፋይናንስ ስርዓቱን ጨምሮ በሁሉም ዘርፎች የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር ያፋጠኑ ስኬቶች መመዝገባቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

ለአብነትም በመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ የሚያደርግ የዲጂታል ስርዓት መፈጠሩን ጠቅሰዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ከአራት ዓመት በፊት ከ50 ቢሊዬን ብር በታች የነበረው የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር አሁን ላይ 9 ነጥብ 7 ትሪሊዬን ብር መድረሱን አብስረዋል።

የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ኢትዮጵያን ከዘመኑ የኢንዱስትሪ አብዮት ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የሚያሸጋግር የዲጂታል ስትራቴጂ በልፅጎ ገቢራዊ ይደረጋልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026