ድሬደዋ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ በድሬደዋ አስተዳደር በተፋሰሰ ልማት ላይ የታየውን የተቀናጀ ብርቱ ተሳትፎ በመኸር እርሻ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ።
በድሬደዋ ገጠር ቀበሌዎች ለአንድ ወር የተካሄደው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።
ከንቲባ ከድር ጁሃር በልማቱ ላይ ግንባር ቀደም ውጤት ላስመዘገቡ 12 ቀበሌዎች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል።
ከንቲባው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ በተፋሰስ ልማት ላይ የታየው የተቀናጀ ውጤት በአጭር ጊዜ የገጠሩን ህብረተሰብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚቻል ማሳያ ሆኗል።
በተፋሰስ ልማቱ የታየውን የተቀናጀ ተሳትፎ በመኸር እርሻም በመድገም የገጠሩን ህብረተሰብ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው ዘንድሮ በ5 ሺህ 550 ሄክታር መሬት ላይ የተቀናጀ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በልማቱ ላይ ከ42 ሺህ በላይ የገጠር ነዋሪዎች በመሳተፍ 99 በመቶ የሚሆነውን ዕቅድ በላቀ ውጤት መፈፀማቸውን አስታውቀዋል።
በተከናወኑ ስራዎች ለተሳትፎ አካላት በሙሉ ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ደግሞ ትራክር እና የውሃ መሳቢያ ሞተር ጀነሬተር መበርከቱን ተናግረዋል።
በገጠር ቀበሌዎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025