አዲስ አበባ፣ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጥሪ አቀረቡ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ ፎረም በብራዚል መዲና ብራዚሊያ ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የብራዚል ኩባንያዎች፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኖች ተገኝተዋል።
ኩባንያዎቹ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን እና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።
አምባሳደር ምስጋኑ በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን ፣ቱሪዝም እንዲሁም በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽንስ ቴክኖሎጂ (አይ ሲቲ) ዘርፎች ትኩረት በሰጠቻቸው ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ መፍጠሩን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ ሳቢ የኢንቨስትመንት ፓኬጆች፣ ምቹ ፖሊሲዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የገበያ ተደራሽነቱን ይበልጥ እንዳሰፋው አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ሳኦ ፖሊ ከተሞች መካከል ያለው ዕለታዊ በረራ የብራዚል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ምቹ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የብራዚል ኩባንያዎች የኢትዮጵያን አዋጪ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በፎረሙ ላይ የተሳተፉ የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ የማድረግ ፍላጎት እንዳደረባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ እና ቱሪዝም ልውውጦች ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025