
አዳማ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፦ የግብርና ናሙና ቆጠራ በግብርና ሀብት ወሳኝ ግብዓቶችን በማሰባሰብ የዘርፉን ዘላቂ ዕድገት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተገለፀ።
ብሔራዊ የግብርና ናሙና ቆጠራ ሂደት የስድስት ወራት አፈፃፀምና ቀጣይ የሚካሄደው የግል እርሻዎች ቆጠራ ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በቆጠራው የስታቲስቲክስ አገልግሎትን ጨምሮ የግብርና ሚኒስቴር፣ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፈዋል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) እንደገለፁት የግብርና ናሙና ቆጠራ ከ22 ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የግብርና ሀብቱ ያለበትን ሁኔታና ደረጃ ለማወቅ እየተካሄደ ይገኛል።
የመረጃ አሰባሰብ ታማኝነትና ትክክለኛነትን እውን ለማድረግ የቴክኒክና ሎጀስቲክ ድጋፍ በማድረግ በአገሪቱ ክልሎች የገጠር ቀበሌዎችና ከተሞች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር)፤ ቆጠራው የግብርና ሀብት ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በዚህም የግብርና ሀብቱ ያለበትን ደረጃና ሁኔታ በማወቅ ለዘርፉ ፖሊስና ስትራቴጂዎች በግብዓት በመጠቀም ግብርናን በሳይንሳዊ አሰራር ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
በቀጣይ የግብርና ሀብት ልማትና እድገት ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በረከት ፍሰሃፅዮን በበኩላቸው በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ፣ ስትራቴጅና የልማት ፕሮግራምን ለማከናወን ቆጠራው ወሳኝ ነው ብለዋል።

የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ለሀብት ምደባ፣ ለመሬት አጠቃቀም፣ ለሰብልና የእንስሳት ሀብት ልማት እድገት መረጃው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወቅታዊ፣ ትክክለኛና አስተማማኝ የግብርና ሀብት መረጃ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለመጨመርና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ፣ የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ያስችላል።
እየተከሄደ ያለው የግብርና ናሙና ቆጠራና በቀጣይ ለሚከናወነው የግል እርሻዎች ቆጠራ ውጤታማነት በትብብር ይሰራል ብለዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026