አዲስ አበባ፤የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፡- የማይበገር የምግብ ስርዓት ፕሮግራም (FSRP) አፈጻጸም ላይ የሚመከር ከፍተኛ የምክክር መድረክ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይደረጋል።
ሁነቱን የዓለም ባንክ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል (CCARDESA) በጋራ በመሆን ያዘጋጀው ነው።
የከፍተኛ ምክክር መድረኩ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናዎች እየተተገበረ የሚገኘው የማይበገር የምግብ ስርዓት ፕሮግራም (FSRP) አፈጻጸም ላይ እንደሚወያይ ኢዜአ ከኢጋድ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካን የምግብ ስርዓት በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የማጠናከር ስራዎች ላይ ያጋጠሙ ፈናተዎች፣እድሎች እና አፈጻጸሙን የሚያሻሽሉ ስትራቴጂዎች ላይ ምክክር ይደረጋል።
የንግድ ትስስር እና የግብርና ፖሊሲዎች፣ ምርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎች እና ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን ማጎልበት ሌሎች ውይይት የሚደረግባቸው አጀንዳዎች ናቸው።
የዓለም ባንክ የማይበገር የምግብ ስርዓት ኢንቨስትመንት እና ፕሮግራሙን እየተገበሩ ያሉ ሀገራት ተሞክሮዎች በውይይቱ ላይ ይቀርባሉ።
የማይበገር የምግብ ስርዓት ፕሮግራም ከፍተኛ የምክክር መድረክ እስከ የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025