
ሮቤ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አሰጣጥን ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ በየደረጃው ለሚገኙ ተቋማት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው ከባሌ ዞን አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በወረዳና ቀበሌ ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በሮቤ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

በሥልጠናው ላይ የተገኙት የዩኒቨርስቲው ተመራማሪና ከፍተኛ አማካሪ ተሰማ አብዲሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የክልሉ ህዝብ ከመንግስት የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኝ ጥናቶች ሲደረጉ ቆይቷል።
በተደረገው ጥናት መሰረትም የሚታዩ ተግዳሮቶችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላትጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ ህዝቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላትን አቅም ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።
እንደ ከፍተኛ ተመራማሪው ገለጻ በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ደረጃ የሚገኙ የአመራር አባላት በአካባቢያቸው የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና አማራጮችን እንዲለዩ ሥልጠናው እገዛ እንደሚኖረው አክለዋል።
ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በኢንተርፕሩነርሽፕና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰነዶች ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይደረጋል ነው ያሉት።
የባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም ኃይሌ በበኩላቸው በዞኑ የሚገኙ 190 ቀበሌዎች በአዲስ አደረጃጀት ተዋቅረው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ የቀበሌ አደረጃጀት አገልግሎት ተግባራዊ እንዲሆን ከ1 ሺህ 300 አመራሮች በላይ ተመድበው ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡
በአገልግሎቱም ከዚህ በፊት ወደ ዞንና ወረዳዎች በተደጋጋሚ ይመጡ የነበሩ ቅሬታዎች እየቀነሱ መምጣታቸውን አመልክተዋል።
በቀበሌ ደረጃ የተጀመረው የአገልግሎት አሰጣጥ ዘላቂ እንዲሆን በየአካባቢው ለተመደቡ አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026