
አዲስ አበባ፤የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፦በካፒታል ገበያ የፋይናንስ ስርዓት ውስጥ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ገለጹ።
'የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት፣ በፋይናንስ ስርዓት ውስጥ የማካተት እና የካፒታል ገበያዎች' በሚል ርዕስ አለማቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ አውደጥናት ተካሒዷል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በወቅቱ እንዳሉት መንግስት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼው ጊዜ በበለጠ እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የኢኮኖሚ እድገትን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ቀርጻ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥም ሴቶች ለአገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
በቅርቡ የተጀመረው የካፒታል ገበያ ስርዓት ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ዕድሎችን በማቅረብ የንግድ ሥራ ዕድገትን እና ፈጠራን ለማጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
መንግስት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ይበልጥ አሳታፊና አካታች የኢኮኖሚ ስርዓትን ለመፍጠር ካቀደው ግብ ጋር ተያይዞ ለስርዓተ-ፆታ ምላሽ የሚሰጥ እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግና የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ለማሸነፍ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የፋይናሻለ ሴክተር ዲፕኒግ ኢትዮጵያ(FSD) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሒክመት አብደላ በበኩላቸው፥ የሴቶችን የፋይናሻል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚሰሩ ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸው አንስተዋል።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀው አለም አቀፉን የሴቶችን ቀንን ከማክበር ባለፈ በፋይናንስ ዘርፉ በተሻለ መልኩ በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቀት በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የስርዓተ ጾታ ልዩነቶች ትኩረት የሚፈልጉ መሆኑን አንስተው ለዚህም የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የፋይናሻል ተቋማት በትብብር መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
የዓለም ባንክ የኢንቨስትመንት ዋና ኃላፊ ግሬሲ ኪዩኮንዳ በበኩላቸው፤ ባንኩ አካታች የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረተ ልማት ግንባታን ለመደገፍ ጠንካራ አቋም እንዳለው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ የሴቶችን የፋይናንስ ተደራሽነት በማስፋትና ንግዱን በማሳደግ ክፍተቱን መዝጋት ይቻላል ብለዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026