አዳማ ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- የአዳማ ከተማ አስተዳደር በምግብ ዋስትና ፕሮግራም የታቀፉ ወገኖች ኑሮ ይበልጥ እንዲሻሻል የሚያደርገውን ድጋፍና እገዛ እንደሚቀጥል የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ ገለጹ።
በፕሮግራሙ ታቅፈው ባለፉት ሶስት ዓመታት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሰማራት ውጤታማ የሆኑ 2ሺህ 969 ወገኖች ዛሬ በአዳማ ተመርቀዋል።
እነዚህ ወገኖች በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ፣በከተማ ግብርና ፣ በተፋሰስ ልማት፣ በፅዳትና ውበት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩ መሆናቸው ተመልክቷል።
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በወቅቱ፤ አስተዳደሩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሻገር አለብን በሚል መርህ የተለያዩ ኢንሼቲቮችና የልማት ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ተግባራዊ እየተደረጉ ካሉት ኢንሼቲቮች መካከል ሰፋፊ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ የወተት ላሞችና የዶሮ ዕርባታ፣ ንብ ማነብ፣ የስጋ ከብቶች ማድለብ፣ እርሻና ንግድ ስራዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ።
በፕሮግራም ታቅፈው ውጤታማ የሆኑት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆኑ አውሰተው፤ በቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ፣ ክህሎትና የቁጣባ ባህላቸው ዳብሮ ዛሬ ለምረቃ በቅተዋል ብለዋል ።
በተለይ በከተማዋ የስራ አጥነትን ለመቀነስና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ኢንሼቲቭ በመቅረጽ ከተረጂነትና ጠባቂነት ለማላቀቅ ከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።
በፕሮግራሙ ታቅፈው ውጤታማ በመሆን የተመረቁት ወገኖች ስራቸውን እንዲያጠናክሩ በስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት በኩል ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ከንቲባው አስታውቀዋል።
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ከዲጃ ጀማል በበኩላቸው፤ የምግብ ዋስትናን በከተማው ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች ተመልምለው በፕሮግራሙ የታቀፉ 2ሺህ 969 ወገኖች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ውጤታማ የሆኑትም የቁጠባ ባህል በማጎልበት በእንስሳት ማድለብ ፣ በወተት ልማት፣ በዶሮ እርባታ ፣ በንግድና በተለያዩ ሙያዎች ተሰማርተው ጠንከረው በመስራታቸው እንደሆነ አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025