
ሸገር፤ የካቲት 29/2017 (ኢዜአ)፡- የሴቶችን አቅም በመገንባት በሁሉም ዘርፎች ንቁ ተሳትፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በተሰራው ስራ ውጤት ተመዝግቧል።
አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ በሴቶች የለሙ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።
በበዓሉ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ የኦሮሚያ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፤ የሸገር ከተማ ከንቲባና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በሸገር ከተማ የተጎበኙት የሴቶች ልማት ስራዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድልን መፍጠር ያስቻሉ ናቸው።

ከዚህም ባለፈ ሴቶች በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ፣ በመሪነት፣ በዲፕሎማሲ፤ በግጭት አፈታትና በሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መብራት ባጫ በበኩላቸው ሴቶች በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ ንቁ ታሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰራቱን ተናግረዋል።
ይህም በክልሉ የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት እያደገ እንዲመጣና በለውጡ የራሳቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ማስቻሉን አስታውቀዋል።
የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በበኩላቸው አስተዳደሩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በመገንባት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት በመስራት ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ አስተዳደሩ የብድር አገልግሎትን በማመቻቸት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉንም አንስተዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026