ድሬዳዋ፤ የካቲት 30/2017(ኢዜአ)፦ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የመሸጫና የማምረቻ ስፍራ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለፀ።
በ20 ሚሊዮን ብር በጀት የተገነባው የመሸጫና የምርት ማሳያ ማዕከል በጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች ለተሰማሩ አምራቾች ዛሬ በዕጣ ተከፋፍሏል ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር፤ በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት አስተዳደሩ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በራስ አቅም የመመለስ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።
በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችን በመገንባት በርካታዎቹን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቀዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን በጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች የተሰማሩ ግለሰቦችን ጥያቄዎች ለመመለስ በከተማዋ የተለያዩ ስፍራዎች የገበያ ማዕከላት ገንብተው ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
በዛሬው ዕለት በ20 ሚሊዮን ብር የተገነባውና ለ29 ሰዎች የተላለፈው የገበያ ማዕከላት የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆኑን በመግለፅ።
በቀጣይም የሌሎቹን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዕጣው የደረሳቸው ግለሰቦች በበኩላቸው በጀመሩት ሥራ ውጤታማ ለመሆን ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ወጣት አብዱልከሪም ሁሴንና ወይዘሮ ዘኪያ ሙሳ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ራሳቸውን በመለወጥና ለሌሎች ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚተጉ ገልጸዋል።
ዛሬ በተካሄደው የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ላይ 69 በጥቃቅንና አነስተኛ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ዕጣ የወጣላቸው 29 ሰዎች የመሸጫና የምርት ማሳያ ማዕከል ተጠቃሚ ሆነዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025