
ድሬዳዋ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፡- መከላከያ የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ከመወጣት ባለፈ ፕሮጀከቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ የሚያስችል ትልቅ አቅም መፍጠሩን በመከላከያ ሚኒስቴር የመሐንዲስ ዋና መምሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ምስጋናው አያሌው ተናገሩ።
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስራ ተቋራጭነትና በመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ባለቤትነት በድሬደዳዋ እና ጎዴ ከተሞች የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከነገ በስቲያ እንደሚመረቁ ተመላክቷል።
ሌተናል ኮሎኔል ምስጋናው አያሌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ መከላከያ የተጣለበትን የሀገር ሉአላዊነትና ዳር ድንበር የማስከበር ተልዕኮ በላቀ ብቃት የመፈጸሙን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል።
ከዚህ ጎን ለጎን የግንባታ ፕሮጀክቶችን በጥራት፣ በፍጥነትና በተያዘላቸው በጀት በማጠናቀቅ በሀገር ግንባታ ላይ የድርሻውን እያበረከተ መሆኑን በመጥቀስ።
ለአብነት በድሬዳዋና በጎዴ ከተሞች የገነባቸው ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ የለውጥ ውጤቶች መሆናቸውን ሌተናል ኮሎኔል ምስጋናው ተናግረዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች ከነገ በስትያ እንደሚመረቁ ጠቁመዋል።
መምሪያው በድሬዳዋ አስመርቆ ከሚያስረክባቸው ፕሮጀክቶች መካከል ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡት ከባለ አንድ መኝታ እስከ ባለ ሶስት መኝታ ክፍሎች ያላቸው 20 ባለ አራት ወለል የምስራቅ ዕዝ የመኖሪያ አፓርትመንት ይገኙበታል ብለዋል።
በተጨማሪም ለሠራዊቱ ዘመኑን የሚመጥን የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚችለው የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ሌላኛው ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው፤ ቪላ ቤቶችን ያካተተው የምስራቅ ዕዝ የመኖሪያ መንደር እንደሚገኝበትም ገልፀዋል።
በጎዴ ከተማ የሚመረቁ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ነው የገለጹት።
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የድሬዳዋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር እንዳልካቸው ታዬ በበኩላቸው፤ እስካሁን ባለው ሂደት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡት 20 ብሎክ የመኖሪያ አፓርትመንት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ናቸው።
የአካባቢው የንግድ ማህበረሰብ በግንባታው ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ሆኗል፤ ሠራዊቱም ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ፍቅርና አንድነት አፅንቶበታል ነው ያሉት።
በግንባታው ሂደትም ከሶስት ሺህ በላይ ሰዎች የስራ ዕድል ማግኘታቸውንም ተናግረዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026