አዲስ አበባ፤ መጋቢት 03/2017(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን የባህልና የጥበብ ስራዎችን በመጠቀም የአገር ገጽታን ሊያጎሉ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ "ባህልና ጥበባት ለቀጣናዊ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር" በሚል መሪ ሀሳብ ከመጪው መጋቢት 11 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ሁለተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ጥበባት ፌስቲቫል ታዘጋጃለች።
ፌስቲቫሉን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ቅድሚያ ለጎረቤት ትሰጣለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት አንስተው፤ ይህን ትስስር የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።
ከጎረቤት አገራት ጋር ያለውን ተመሳሳይ ባህል ለበጎ ተግባር መጠቀምና የቀጣናውን ልማት ማፋጠን እንደሚገባም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር በመንገድ፣ በባቡር በኤሌክትሪክና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች ትስስር መፍጠሯ በጋራ የማደግ ፍላጎቷ ማሳያ ነው ብለዋል።
የቀጣናውን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ባህልና ኪነ ጥበብ ቁልፍ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።
ባህልና ኪነ ጥበብ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን የበለጠ እንዲያጠናክሩ መገናኛ ብዙሃን ከተለመደው ዘገባ ባለፈ ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት መዘገብና ማስተዋወቅ አለባቸው ብለዋል።
መገናኛ ብዙሃን የአገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚያስጠብቁ አጀንዳዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝና የአገርን ገፅታ የሚያስተዋውቁ ዘገባዎችን መስራት እንዳለባቸውም አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025