አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የመዲናዋን የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች በተመለከተ ከነዋሪዎች ጥሪ መቀበል የሚያስችል የጥሪ ማዕከልን ጨምሮ የተለያዩ 10 ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደርጓል።
ፀጥታን የተመለከቱ ጥቆማና ቅሬታ፣ በማንኛውም የከተማዋ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እና በቢሮው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መረጃ መስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ነው ቢሮው ዛሬ ይፋ ያደረገው።
በዚህም ቢሮው 8882 የነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል፣ የድረ ገጽ፣ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ፣ አሴት ማኔጅመንት፣ ቪዲዮ ኮንፍረንስን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ስራዎችን ይፋ አድርጓል።
ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለማቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማስተዋወቅና ለማስጀመር የተዘጋጀ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በቢሮው የለሙትን ቴክኖሎጂዎች ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ባለፉት ዓመታት ህዝቡን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች የከተማዋን ሰላም ዘላቂ ማድረግ ተችሏል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025