የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛ ምዕራፍ እየለሙ የሚገኙ ስምንት ኮሪደሮች የስራ አፈጻጸም ተገመገመ

Mar 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛ ምዕራፍ እየለሙ የሚገኙ ስምንት ኮሪደሮች የስራ አፈጻጸም መገምገሙን የመዲናዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ላለፉት ሁለት ቀናት ከሁሉም የኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች ጋር በመሆን በ2ኛ ምዕራፍ በከተማችን እየለሙ የሚገኙ ስምንት ኮሪደሮችን የስራ አፈጻጸም ተዘዋውረን ገምግመናል ብለዋል።


የ2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ 135 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገድ ግንባታ፣ 42 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ፣ 431 ሄክታር የሚሸፍን የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ በከተማችን ያለውን የትራንስፖርት ስርዓት ለማዘመን ከምንሰራው ስራ በተጨማሪ 23,320 በላይ መኪኖችን የማስቆም አቅም ያለው የፓርኪንግና ተርሚናሎች ግንባታ፣ 112 የህዝብ የመጸዳጃ ቦታዎች ግንባታ፣ 2669 ህንጻዎች እድሳት፣ የህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን ያካተተ ሲሆን ከ62ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ደግሞ የስራ እድልን የፈጠረ ሰፊ ስራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ከተማውን በመበከል የህዝቡን ጤና በመጉዳት ከፍተኛ አሉታዊ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩትን ህግ እና ስርዓት አውጥተን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየተገበርን ነው ሲሉም አክለዋል።

የወንዞችን ብክለት በመከላከል በኩል ጽዱ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ለመፍጠር የብክለት መከላከል ህግ ህብረተሰባችን መቀበሉን እና እየተገበረው መሆኑን በጉብኝታችን ወቅት ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል።


በተሰጣቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ያልገነቡ እና የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታቸውን ያላስተካከሉትን በመቅጣት ላይ የምንገኝ ሲሆን ከቅጣቱ በላይ የምንፈልገው ህዝባችን በዋናነት ለራሱ ጤና ሲል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓቱን እና ብክለት መከላከልን እንዲተገብር በመሆኑ ሁላችንም ለዚህ ርብርብ እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመቀበል ህንጻዎችን በማደስ፣ ቀለም በመቀየር እና በከተማዋ ስታንዳርድ መሰረት መብራት በመዘርጋት እያገዙን የሚገኙ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም የመንግስትና የግል ተቋማትን ጨምሮ ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉልን የሚገኙ ነዋሪዎቻችንን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ ነው ያሉት።

በቀሪ ጊዜያት ልዩ ክትትል በማድረግ ቶሎ መጠናቅ ያለባቸውን ስራዎች መጨረስ፣ መደገፍ የሚገባቸውን ደግሞ እየደገፍን ህዝባችንን በታማኝነት ለማገልገል በገባነው ቃል መሰረት 2ኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት አጠናቅቀን ለግልጋሎት ክፍት የምናደርግ ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026