
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በልግ አብቃይ አካባቢዎች ለበልግ እርሻ ልማት አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ባሪሶ ፋይሳ እንዳሉት በዘንድሮ የበልግ ወቅት አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት ከ40 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በዚህ ወቅት በዘር ለመሸፈን ከታቀደው ውስጥ እስካሁን አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ በሁሉም በልግ አብቃይ በሆኑ ዞኖች የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እየተጓጓዝ መሆኑን ገልጸዋል።
ቢሮው ባለፉት ዓመታት ከነበሩት ክፍተቶች ልምድ በመውሰድ ከባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ጋር ውይይት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
በዚህም በዘንድሮ ዓመት ማሟላት የሚገቡ ክፍተቶች ተለይተው ወደ ስራ መገባቱን አመልክተው ቀጣይ ዘር መዝራትና የሰብል እንክብካቤና ጥበቃ ተከታታይ ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
በዚህ ዓመት በተለየ ሁኔታ ከሁለተኛ ሩብ ዓመት ጀምሮ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በተካሄደ ግምገማ አርሶ አደሩን በማንቃት ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም እንዲችል መደረጉንም አክለዋል።
በማሳ ዝግጅት፣ በአፈር ማዳበሪያ፣ በዘር አያያዝና አጠቃቀም፣ በሰብል እንክብካቤና ጥበቃ በኩል በተሰራው ስራ የአርሶ አደሩ መነቃቃትና ተነሳሽነት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።
አርሶ አደሩ አሁን ላይ ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ የአስተራረስ ስነ-ዘዴ እየተሸጋገረ መምጣቱን አመልክተው ለዚህም 7 ሺህ ትራክተሮች እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል።
ትራክተሮቹም በየአካባቢዎቹ እየተንቀሳቀሱ የሚያርሱ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ አርሶ አደሮቹ በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በኑሮው እየተለወጠ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተያዘው የበልግ ወቅት አርሶ አደሩ፣ ባለሙያውና አመራሩ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ባለው ዝናብ ዘር በመዝራትና በመንከባከብ በኩል ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026