
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከእስራኤል ኤነርጂና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ኤሊ ኮህን ጋር በሁለትዮሽና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በኢነርጂ፣ በማዕድን፤ በመሰረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው።
ሚኒስትሮቹ ሀገራቱ በፖለቲካ እና ደህንነት ዘርፍ ያላቸውን ጠንካራ ትብብር በኢኮኖሚ ዘርፍም ይበልጥ እንዲዳብር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ካላት ሰፊ የታዳሽ ኃይል አቅም አንጻር የእስራኤል ኩባንያዎች መሰማራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያሉ የትብብር አማራጮችን ለመቃኘት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የእስራኤል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት በሚሰማሩበት ሁኔታ እና ሀገሪቷ በመስኖ እና ግብርና ቴክኖሎጂ ያላትን የቴክኖሎጂ አቆም በመጠቀም የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ትብብር መፍጠር እንደሚቻልም አንስተዋል።
የእስራኤል የኢነርጂ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ኢሊ ኮኸን የሀገራቸው መንግስት የእስራኤል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን እንዲጠቀሙ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በቅርቡም በሳቸው የተመራ የንግድ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የትብብር አማራጮችን ማየት የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹም አመልክተዋል።
የእስራኤል የኢነርጂ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ኢሊ ኮኸን እ.አ.አ በፊብሩዋሪ 2025 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤና፣ በምርምር፣ በኢኖቬሽን እና ኤነርጂ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026