
ጋምቤላ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የተተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የእንስሳት ሃብት ልማትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
መርሃ ግብሩ በክልሉ ከተጀመረ ወዲህ በርካታ የወተት፣ የንብ ማነብ፣ የዶሮና የዓሳ መንደሮች መፈጠራቸውንም ቢሮው ገልጿል።
የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ክርሚስ ሌሮ፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የክልሉን የእንስሳት ልማት ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ለኢዜአ ተናግረዋል።
ይህም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባለፈ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዶሮ፣ የወተት፣ የንብ ማነብና የዓሳ መንደሮች እንዲፈጠሩ አስችሏልም ብለዋል።
በክልሉ ጋምቤላ ከተማ፣ ጎደሬ፣ መንጌሽና ጋምቤላ ወረዳዎች በርካታ የንብ ማነቢየ መንደሮች መፈጠራቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በኑዌር ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎችና ሌሎች አካባቢዎች በርካታ የወተት መንደሮች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
የወተት ምርቱን አዘምኖ በመጠቀምና የተሻሻሉ የወተት ላሞችን የማዳቀል ስራ ላይ ለውጦች እንዳሉም ተናግረዋል።
በክልሉ በአኝዋሃና በኑዌር ዞኖችም በስፋት የዓሳ መንደሮች መፈጠራቸውን ጠቁመው፤ ቢሮው በዘርፉ የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።
በክልሉ በዶሮ እርባታ ዘርፍ ከተሰማሩት መካከል አቶ ወንድሙ ባልቻ በሰጡት አስተያየት፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በዘርፉ በመሰማራታቸው ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሩ በዘርፉ ለመሰማራት ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠረላቸው የገለጹት ደግሞ በጎደሬ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ ላይ የተሰማሩት አርሶ አደር ብራሃኑ ገዳሙ ናቸው።
መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ የግብዓት አቅርቦት በማመቻቸቱ የ72 ባህላዊና ዘመናዊ ቀፎዎች ባለቤት መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026