የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የመሪዎችን መተማመንና ብርቱ ትብብር ይጠይቃል- የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋዜጠኞች

Mar 17, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 06/2017(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው ኢዜአ ያነጋገራቸው የቀጣናው ሀገራት ጋዜጠኞች ገለጹ።

ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በቀጣናዊ ሰላም፣ ልማትና ትስስር ዙሪያ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ስቱዲዮ ተወያይተዋል።

ጋዜጠኞቹ በውይይታቸው የቀጣናው ሀገራት መሪዎች በሀገራዊና እና ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በመተማመን ላይ የተመሰረተ ትብብር ማጠናከር እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ኬንያዊ ጋዜጠኛ ናሊስተን ጃጊ ተለዋዋጭ በሆነው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ "ለአፍሪካዊ ችግር፣ አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚለው መርህ መሰረት ለዘላቂ ሰላም መተባበር ይገባል ብሏል።


የደቡብ ሱዳን ጋዜጠኛው ኦባንጅ ኦከች ለቀጣናዊ ችግሮችን ጎረቤት ሀገራት ከማንም በተሻለ በቅርበት መምከርና ለችግሩ እልባት መስጠት እንጂ ሶስተኛ ሩቅ ወገን መጋበዝና ጉዳዩን ማባባስ እንደማይገባቸው ነው ያነሳው።


ኡጋንዳዊት ጋዜጠኛ ዲያና አኩሎ በበኩሉ ሰላምን ለማረጋገጥ ሚዲያ ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅሶ፤ ጋዜጠኞች ግጭትን አባባሽ ሳይሆን ለቀጣናዊ ሰላምና አብሮነት አበክረው እንዲሰሩ ጠይቃለች።


የተዛቡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች ትልቅ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እየፈጠሩ ባሉበት ወቅት ትክክለኛውን መረጃ በወቅቱ ማድረስ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተናግራለች፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025