
ጅማ፣መጋቢት 7/2017(ኢዜአ) ፡-በጅማ ከተማ የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና በ“ኦንላይን” ለተከታተሉ 842 ሰዎች ዛሬ የምስክር ወረቀት ተሰጠ።
የምስክር ወረቀቱ የተሰጣቸው መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ወጣቶችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ።
የኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ስልጠና ዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ ማበልፀግ፣ የዳታ አናላይስስ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጄንስ መሰረታዊ ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ይህም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና በኢትዮጵያ መንግስት የሚተገበር ሲሆን፤ሐምሌ 16 /2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን ለመድረስ ታቅዶ በተጀመረው የ”ኦንላይን” ስልጠና መረሃ ግብር የዲጂታል ማህበረሰብን በመፍጠር አሰራርንና አገልግሎትን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ተመልክቷል።
በጅማ ከተማ በ“ኦንላይን” ስልጠናውን ተከታትላው ዛሬ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ወጣቶችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች የዚሁ መረሃ ግብር አካል ናቸው።
በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ግርማ ባይሳ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀረጸው የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ፕሮግራም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ብለዋል።
የመማር ማስተማር ሂደትን ለማቀላጠፍና የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑን አመልክተው፥ እድሉን በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና በ”ኦንላይን” ለመስጠት ከታቀደው ውስጥ እስካሁን ለ500ሺህ ሰዎች መሰጠቱን ጠቁመዋል።
የጅማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው፥በጅማ ከተማ የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ተከታትለው ዛሬ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ወጣቶችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያውያን ኮደርስ በዲጂታል የተደገፈ የአሰራር ስርዓትን ለመፍጠር ታስቦ የተቀረጸ መሆኑን አንስተዋል።
ከሰልጣኞቹ መካከል የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህር ብርሃኑ መንግስቱ በሰጡት አስተያየት፥ አንድሮይድ ማበልፀግ እና የዳታ አናላይስስ ስልጠና ወስጄ እውቀት አግኝቼበታለው ብለዋል።
የኮሚኒቲ ስኩል ተማሪ ቀነኒ ታደሰ በበኩሉ፤ የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠናው ከዲጂታል ዓለም ጋር በመተዋወቅ በቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለመሆን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረለት ገልጿል።
በጅማ ከተማ በተመሳሳይ ስልጠናውን የሚከታተሉ ሌሎችም ሰዎች በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026