ባህር ዳር፤መጋቢት 7/2017 (ኢዜአ)፦በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋ ገና ብዙ መገለጥ የሚችሉ ውበቶችን በተፈጥሮ የታደለች ሳቢና ማራኪ ከተማ መሆኗን ያሳዩ ናቸው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
በባህር ዳር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በፌዴራልና በክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ዛሬ ተጎብኝተዋል።
ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት፥ ባህር ዳር ገና ብዙ መገለጥ የሚችሉ ውበቶችን በተፈጥሮ የታደለች ሳቢና ማራኪ ከተማ ነች።
ከተማዋ በከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የምትገኝ መሆኗን ገልፀው፥ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደተመለከቱም ተናግረዋል።
ይህም የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ ከማድረግ ባለፈ ከጣና ኃይቅ ጋር የሚያገናኙ መንገዶች በ7 ቦታዎች ተከፍተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልፀዋል።
ይህም ለከተማዋ ነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ጣናን በቀላሉ የሚያይበትን ዕድል እንዲፈጠር ማድረጉንም አመልክተዋል።
እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ ህንፃዎች እየታደሱና ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን የሚያጎናፅፍ የቀለም ኮድ እየተተገበረ መሆኑ ለከተማዋ ተደማሪ ውበትና ድምቀት ማላበሱንም አስረድተዋል።
የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት አጉልቶ በማውጣት ዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነቷን ለማሳደግ በቀጣይም ስራው ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ በ ''8 ሪጂዮ ፖሊታን'' ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራዎች ሌት ተቀን እየተከናወኑ ነው።
የኮሪደር ልማቱ የስራ ባህልን ከመቀየሩም በላይ በተለይ በጣና ዳርቻ የተከፈቱ ቦታዎች ነዋሪዎችና ከሌላ ቦታ የመጡ እንግዶች ያለምንም ስጋት እየተዝናኑ እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ ይዞት የመጣው መልካም ነገር ያሉንን ሃብቶችና ፀጋዎች በአግባቡ አልምተን በመጠቀም የከተሞችን እድገት እንድናፋጥን አድርጓል ብለዋል።
በቀጣይም የከተሞችን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን የኮሪደርና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በጥራትና በፍጥነት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ በበኩላቸው፥ ለባህር ዳር ከተማ የውበት መገለጫ ከሆኑ ዘንባባዎቿ ጋር የሚያምር የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን መታዘባቸውን ገልጸዋል።
የተረጋጋ ሰላም በከተማዋ በመኖሩም በርካታ የህብረተሰብ ክፍል በኮሪደር ልማቱ በጣና ዳርቻ በተከፈቱ መንገዶች ከነቤተሰባቸው እየተዝናኑ መሆኑን ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅት ወደ ባህር ዳር መጥቶ ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሃብት በቀጣይ ያማረ ፍሬን ይበላል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከተማዋ ለዚህ የተመቸች ውብና ማራኪ መሆኗን አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025