የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት መስመር ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ

Mar 18, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፡-በደሴ ከተማ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት መስመር ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ።


የክልልና የደሴ ከተማ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት የደሴ ከተማን ኮሪደርን ጨምሮ ሌሎችንም መሰረተ ልማቶች ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡


በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም አበራ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የኮሪደር ልማቱ በተያዘለት ጊዜ በጥራት እየተሰራ ነው፡፡


በተለይ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት መቻሉ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ጠቁመው፤በኮሪደር ልማቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራው በአብዛኛው ተጠናቆ አስፋልት ማንጠፍ እንደተጀመረ ገልጸዋል፡፡


ለበርካታ ወገኖችም የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።


የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሱለይማን እሸቱ በበኩላቸው፤ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ይበልጥ ውብና ለነዋሪዎች ምቹ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።


የደሴ ከተማ የኮሪደር ልማትም በፍጥነትና በጥራት እየተከናወነ መሆኑን ዛሬ በመስክ ምልከታ አረጋግጠናል ብለዋል፡፡


በተለይ ህብረተሰቡን በማሳተፍና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማቱ ለሌሎች ከተሞችም ምሳሌ በመሆን ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


በልማቱ የብስክሌትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ሌሎቸንም አረንጓዴ ሥፍራዎችና መዝነኛዎች እየተሰሩ በመሆኑ ተደስተናል ያሉት አቶ ሱለይማን፤ ክልሉም ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል፡፡


በደሴ የኮሪደር ልማቱ ከቧንቧ ውሃ-ሮቢት- ወሎ ባህል አምባ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚጠጋ መንገድ እንደሚሸፍን ታውቋል፡፡


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026