የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአስተዳደሩ በጀነሬተር ሲሰሩ የነበሩ የውሃ ተቋማት በሐሀይ ሀይል እንዲሰሩ በመደረጉ የውሃ አቅርቦቱ ተሻሽሏል

Mar 18, 2025

IDOPRESS

ሰቆጣ፤መጋቢት 8/2017 (ኢዜአ)፦በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በጀነሬተር የሚሰሩ የውሃ ተቋማት በፀሐይ ሀይል እንዲሰሩ በመደረጉ የውሃ አቅርቦቱ መሻሻሉን የአስተዳደሩ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ።


የመምሪያው ሃላፊ ዲያቆን አብርሃም አሰፋ ለኢዜአ እንደገለጹት በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተገነቡት አብዛኞቹ የውሃ ተቋማት በጀኔሬተርና በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ናቸው።


እነዚህ ተቋማት የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ሲደረግና የኤሌክትሪክ ሀይል ሲቋረጥ የሚቆሙበት ሁኔታ እንዳለ ገልጸው፣ በዚህም ህብረተሰቡ የወንዝ ውሃን ለመቅዳት ጊዜና ጉልበቱን ያባክን እንደነበር አውስተዋል።


ባለፉት ሰባት ወራትም ችግሩን በመሰረታዊነት ለመፍታ ስምንት የውሃ ተቋማትን ወደ ጸሐይ ሀይል በመቀየር የውሃ አቅርቦት እንዲጠናከር መሰራቱን ገልጸዋል።


በዚህም ከ80 ሚሊዮን 256 ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ የሀይል አቅርቦቱን ወደ ጸሐይ ሀይል መቀየሩን ገልጸዋል።


በዚህም 86ሺህ 484 የህብረተሰብ ክፍሎችን ያልተቋረጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን መምሪያ ሃላፊው አስረድተዋል።


በአሁኑ ወቅትም በጋዝጊብላና ሰሃላ ወረዳዎች ያሉ የውሃ ተቋማትኝ በጸሐይ ሀይል እንዲሰሩ የማድረግ ሥራው እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።


በአበርገሌ ወረዳ የኒሯቅ ከተማ የሚኖሩት አቶ ገብሬ ሚሰነ እንደገለጹት በአካባቢያቸው ያለው የውሃ ተቋም በጸሐይ ሀይል እንዲሰራ ከተደረገ ወዲህ የመጠጥ ውሃ ሳይቋረጥ እያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል።


በአካባቢያቸው የተሰራው የጸሐይ ሀይል ማመንጫም በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጥም አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ሌላዋ የእዚሁ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ሰርካለም ሃላዩ በበኩላቸው፣ የአካባቢያቸው የውሃ ተቋም በጸሐይ ሀይል መስራት ከጀመረ ወዲህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ መሻሻሉን ነው የገለጹት።


"ከዚህ ቀደም በኤሌክትሪክ ሀይል ይሰራ የነበረው የውሃ ተቋሙ ሀይል ሲቋረጥ አገልግሎቱም አብሮ ስለሚቋረጥ የወንዝ ውሃ ለመጠቀም እንገደድ ነበር" ብለዋል።


በእዚህም ለውሃ ወለድና ሌሎች በሽታዎች ይጋለጡ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ችግራቸው መፈታቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026