የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ስለ ባሕርዳር ከተማ ምን አሉ?

Mar 18, 2025

IDOPRESS

ተፈጥሮ እና የሰው ጥበብ ተዋሕደው የባሕር ዳርን ውበት ይበልጥ እያወጡት ነው።

ከተማዋን የንግድና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አመራሩ እየጣረ ነው።

ባሕር ዳር በፈተና ውስጥ የመጽናት ምሳሌ ናት፤ ባለፉት ዓመታት የነበረው ፈተና እያለፈ ነው። ባሕር ዳር በፈተናው ውስጥ ሥራዋን አላቋረጠችም።

ለፈተና የተወረወረውን ድንጋይ ለግንባታ ተጠቅማበታለች።

የጣና መከፈት የማስተሣሠር(ኮኔክቲቪቲ) መርሐችን መገለጫ ነው።

የልማት ሥራዎቻችን መመጋገብ እና መተሣሠር እንዳለባቸው የባሕር ዳር ኮሪደር ምሳሌ ይሆናል።

ለብዙ ዘመናት ከከተማው ተለያይቶ የነበረው ጣና ወደ ስምንት በሚደርሱ ቦታዎች ከኮሪደሩ ጋር ተገናኝቷል። ይህም ከመዝናኛነቱ ባሻገር ከተማዋን ነፋሻማ አድርጓታል።

በመደመር መንገድ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በነባር ዕሴቶቻችን ላይ አዳዲስ ዕሴቶችን ጨምረን መገንባት አለብን።

ባሕርዳር የጣና ሐይቅና የዓባይ ወንዝ መገናኛ ናት።

ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የዘንባባ ዛፎች አሏት። በዚህ ላይ የኮሪደር ልማቱ ለባሕር ዳር ተጨማሪ ውበት ሰጥቷታል።

የአካባቢ ተቋማት ፈጠራ እየጨመሩ ልማትን እንዲያሣልጡ ማድረግ፤

በባሕር ዳር ኮሪደር የለበሱት ንጣፎች እና የቆሙት መብራቶች በአካባቢው ተቋማትና ባለሞያዎች የተዘጋጁ ናቸው።

በቀጣይም አካባቢያዊ ክሂሎትንና ዐቅምን መጠቀም የበለጠ መለመድ አለበት።

ባሕርዳርን የስፖርትና የቅርስ ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፦ በጣና ዙሪያ ያሉት ታሪካዊ ሥፍራዎች፤ ከጣናና ከዓባይ ጋር ተያይዘው የተሠሩት ወደቦችና መናፈሻዎች፤ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የዓባይ ዘመናዊ ድልድይ እና ሌሎቹም ልማቶች ባሕር ዳርን የ22ኛው መክዘ የንግድና ቱሪዝም ማዕከል እያደረጓት ነው።

የአመራር አርአያነት፦ አመራር ሠርቶ የሚያሠራ፣ ቀድሞ የሚያስከትል መሆን አለበት።

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የራሳቸውን ጽህፈት ቤት አካባቢ አስተካክለው ኮሪደሩን በመሥራት አርአያ መሆናቸው ትምህርት የሚሆን ነው።

ባሕር ዳር ከዚህም በላይ መሥራት የምትችል ናት። ይሄ መጀመሪያዋ እንጂ የመጨረሻዋ አይደለም።

ጽዳቱን ባህል ማድረግ፤ የተሠሩ አካባቢዎችን ጥንቅቅ ማድረግ፤ ተቋማት አካባቢያቸውን እንዲቀይሩ ማትጋት፤ ንግድን፣ ቱሪዝምንና ኢንቨስትመንትን ይበልጥ ማበረታታት፣ ከሕዝቡም ከአመራሩም ይጠበቃል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026