አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ)፦ ዓለም ዲጂታል መልክ በያዘበት በዚህ ዘመን መገናኛ ብዙሃን የዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ ሊሆኑ እንደሚገባ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።
የአማርኛ ፌስቡክ ገጽ ተከታይ 4 ሚሊየን መሻገሩን ተከትሎ “ፋና ሚዲያ ዲጂታል ዐርበኛ” በሚል መሪ ሐሳብ የማበረታቻና ዕውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
አማካሪ ሚኒስትሩና የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የተቋሙ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
አማካሪ ሚኒስትሩና የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በወቅቱ እንዳሉት ዓለም ወደ ዲጂታል በመለወጡ ሚዲያው በድሮ አሰራር ብቻ መቀጠል አይቻልም።
የአዲሱ ትውልዱ ቋንቋ ወደ ዲጂታል ዓለም እየተለወጠ መምጣቱን ጠቅሰው፤ መገናኛ ብዙሃን ዲጂታል ዘርፍ በሁሉም ፕላትፎርሞች ተጠናክሮ መውጣት እንዳለበት አንስተዋል።
ሚዲያ የነገ መልክ የሚቀርጽ በመሆኑ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ዋኝቶ ለመሻገር በዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
እንደ ሀገር የሚዲያዎችን የዲጂታል አቅም ለማጎልበት በሰው ኃይል የማብቃት፣ ተደራሽነትና የቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግ ስራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ተደራሽነትን ለማሳደግ በርካታ ስራዎች በመሰራቱ ዕውቅናው እንደተሰጠ ጠቅሰዋል።
ኢዜአን ጨምሮ ባለፉት ወራት የዲጂታል አቅም ለማጎልበት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፤ ሁሉም ተቋማት በየፊናቸው በፈጣን ለውጥ ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዲጂታል ቡድን የሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን አንስተው፤ ከ4 ሚሊየን የተሻገረ ተከታይ በማፍራታችሁ እንኳን ደስ አላችህ ብለዋል።
የሚዲያ ተቋማት ሕብረት ፈጥረው ፋና ላይ የመጣው ለውጥ ወደ ሌሎች ተቋማትም ሊስፋፋ እንደሚገባው አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ታደሰ፤ የዲጂታል ሚዲያው ዘርፍ በሀገር ግንባታ ውስጥ የድርሻውን እንዲወጣ ሁሉም ሚናውን መጫወት እንዳለበት ጠቁመዋል።
ሁሉንም ሚዲያ አማራጮችና አቅም በማሰባሰብ ጥሩ ውጤት እየመጣ እንደሆነም ገልጸው፤ እንደ ሚዲያ ብንፎካከርም የምንሰራው ለአንድ ሀገር መሆኑ መረሳት የለበትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሳፍንት ተፈራ በበኩላቸው÷ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት አድንቀው፣ በቀጣይም የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ዘመናዊ የሆነው የዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ በባህላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል እንደነበር አንስተው÷ ዘመኑን መስሎ መጓዝ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025