አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):- የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኢትዮጵያ መጀመሪያ የሆነውን የታካሚዎች የሜዲካል ቦርድ የዲጂታል ሰርተፊኬት አገልግሎትን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
ሰርተፍኬቱ በወረቀት ሲሰጥ የነበረውን የታካሚዎች ሜዲካል ቦርድ አሰራር የሚያስቀር ነው።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ እና የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የአገልግሎቱ መጀመር ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ህክምና ለሚፈልጉ ታካሚዎች እንግልት የሚቀንስና የአገልግሎት ፈላጊዎችን እርካታ የሚጨምር መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም የሆስፒታሉን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ የሚያሻሽል እንዲሁም የተሳሳቱ ማስረጃዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አጋዥ እንደሆነ አመልክተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የጤና ሚኒስቴር ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ህክምና ለሚፈልጉ ታካሚዎች ወጥ በሆነ አሰራር ማስተናገድ የሚያስችል መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የሆስፒታሉ ሁሉንም አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሆስፒታሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚጠቀጥል ተናግረዋል።
የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ ሆስፒታሉ የታካሚዎች የሜዲካል ቦርድ የዲጂታል ሰርተፊኬት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የተገልጋዮችን እርካታ እንደሚጨምር ገልጸዋል።
አገልግሎቱ የተጀመሩ የሜዲካል ሪከርድ ስርዓትን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚያግዝም አመልክተዋል።
የዲጂታል ሰርተፍኬቱ ስራ ሌሎች ሆስፒታሎች እና የጤና ተቋማት አገልግሎቱን እንዲጀምሩ በር ከፋች መሆኑንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማሪ ስቶፕስ ኢትዮጵያ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከመወለጃ ቀናቸው አስቀድሞ ለሚወለዱ ጨቅላ ህፃናት ክብካቤ የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ እንዲሁም ለማወለጃ ክፍል እድሳት የሚሆን ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
ዶክተር ደረጀ ድጋፉ የግል እና የመንግስት ተቋማት በትብብር መስራት እንደሚችሉ ማሳያ እንደሆነ መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025